Skip to content
የBible App ዓርማ

ሐዋርያት ሥራ 1:22 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሐዋርያት ሥራ 1:22 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ይኸውም፣ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ ተለይቶ እስካረገበት ቀን ድረስ የነበረ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋራ የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”

ሐዋርያት ሥራ 1:22 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እንዲሁም ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ አብረውን ከነበሩት ከነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”

ሐዋርያት ሥራ 1:22 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእኛ መካ​ከል በገ​ባ​በ​ትና በወ​ጣ​በት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብ​ረው ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የት​ን​ሣ​ኤዉ ምስ​ክር ይሆን ዘንድ ይገ​ባል።”

ሐዋርያት ሥራ 1:21-22 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።

ሐዋርያት ሥራ 1:21-22 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።”