Skip to content

2 ሳሙኤል 5:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

2 ሳሙኤል 5:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በቀደመው ዘመን ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ በነበረ ጊዜ፣ እስራኤልን በጦርነት የምትመራ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፣ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”

2 ሳሙኤል 5:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከአሁን በፊት ሳኦል የእኛ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንኳ በጦርነት እስራኤልን የምትመራ አንተ ነበርክ፤ እንዲሁም ሕዝቡን እስራኤልን እንድትመራና በእስራኤልም ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶልሃል።”

2 ሳሙኤል 5:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

አስ​ቀ​ድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ታ​ወ​ጣና የም​ታ​ገባ አንተ ነበ​ርህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ ትሆ​ና​ለህ ብሎህ” ነበር።

2 ሳሙኤል 5:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፥ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፥ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ ነበር አሉት።

2 ሳሙኤል 5:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”