2 ሳሙኤል 3:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
2 ሳሙኤል 3:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ዳዊት በኬብሮን ሳለ፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ የበኵር ልጁ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን፣
2 ሳሙኤል 3:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ዳዊት በኬብሮን ሳለ ስድስት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥
2 ሳሙኤል 3:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ለዳዊትም ወንዶች ልጆች በኬብሮን ተወለዱለት፤ በኵሩም ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበረ።
2 ሳሙኤል 3:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ለዳዊትም ወንድ ልጆች በኬብሮን ተወለዱለት፥ በኩሩም ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበረ።
2 ሳሙኤል 3:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ዳዊት በኬብሮን እያለ፥ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ የበኲር ልጁ፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥