1
የዮሐንስ ወንጌል 14:27
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይታወክ፤ አይፍራም።
Qhathanisa
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:27
2
የዮሐንስ ወንጌል 14:6
ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:6
3
የዮሐንስ ወንጌል 14:1
“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:1
4
የዮሐንስ ወንጌል 14:26
አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:26
5
የዮሐንስ ወንጌል 14:21
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:21
6
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
እኔም አብን እለምናለሁ፤ ለዘለዓለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ምክንያቱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ነው። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፥ በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
7
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
አብ በወልድ እንዲከብር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
8
የዮሐንስ ወንጌል 14:15
“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:15
9
የዮሐንስ ወንጌል 14:2
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ እላችሁ ነበርን?
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:2
10
የዮሐንስ ወንጌል 14:3
ሄጄም ስፍራ ሳዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትኖሩ ዳግምኛ እመጣለሁ፤ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:3
11
የዮሐንስ ወንጌል 14:5
ቶማስም “ጌታ ሆይ! ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 14:5
Ikhaya
IBhayibheli
Amapulani
Amavidiyo