1
ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እነርሱም እንደገና አብዝተው ጠሉት።
Qhathanisa
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
2
ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፥ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
3
ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ሊያናግሩትም አልቻሉም።
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
4
ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም፦ “እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፥ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ።” ሲል ነገራቸው።
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
5
ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
ወንድሞቹም ቀኑበት፥ አባቱ ግን ነገሩን ጠብቆ አኖረው።
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
6
ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
እርሱም አላቸው፦ “እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፥ እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
7
ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
ኑ፥ እንግደለውና በአንዱ ጉድጓድ ውስጥ እንጣለው፦ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፥ የሕልሞቹን መጨረሻ እናያለን።”
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
8
ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
9
ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፦ “ያ ሕልም አላሚ ይኸው መጣ።
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
10
ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩት፥ ወደ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ።
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
11
ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
“ደም አታፍስሱ፥ በዚህች ምድረ በዳ ባለችው ጉድጓድ ጣሉት፥ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት” አላቸው። እንዲህም ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው።
Hlola ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
Ikhaya
IBhayibheli
Amapulani
Amavidiyo