የማቴዎስ ወንጌል መግቢያ
መግቢያ
ወንጌል የሚለው ቃል መልካም ዜና፥ ብሥራት ወይም የምሥራች ማለት ነው። በዚህም መሠረት የማቴዎስ ወንጌል አስቀድሞ የተነገረለትንና በተስፋ መምጣቱ ሲጠበቅ የነበረውን የኢየሱስን መሢሕነትና አዳኝነት ያበሥራል። ይህም የምሥራች ቃል ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ጭምር ነው።
የኢየሱስ ስብከቶች በማቴዎስ ወንጌል መዋቅር ውስጥ ትልቅ ስፍራ ይይዛሉ። በተለይም የተራራው ስብከት የክርስቲያናዊ ሕይወት መመሪያ ወይም አዲሱ የክርስቶስ ፈቃድ ተብሎ ሊወሰድ ይችላል።
የማቴዎስ ወንጌል ወልድ አምላክ እንደ ሆነ አማኑኤል በማለት ያበስርና ከልደቱ ጀምሮ ስለ ጥምቀቱና ስለ ፈተናው ያብራራል። ከዚያም በገሊላ የፈጸመውን የስብከት፥ የማስተማርና የመፈወስ አገልግሎት ያቀርባል። ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ሕግ ለመተርጎም ሥልጣን ያለው መምህር፥ ዘላለማዊ ንጉሥ፥ በክቡር ደሙ፥ በሕማማቱና በትንሣኤው የአዲስ ኪዳንና ቤተ ክርስቲያንንን መሥራች እንደሆነ ይገልጻል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የኢየሱስ መወለድ (1፥1—2፥23)
የእግዚአብሔር መንግሥት አዋጅና የተራራው ስብከት (3፥1—7፥29)
የሐዋርያቱ መመረጥ፥ መላክና የተልእኮ መመሪያ (8፥1—11፥1)
ከእስራኤል የገጠመው ተቃውሞና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ምሳሌዎች (11፥2—13፥53)
ኢየሱስ፥ የእግዚአብሔር መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን (13፥54—18፥35)
በይሁዳና በኢየሩሳሌም የነበረው ተልእኮ (19፥1—25፥46)
ሕማማቱናና ትንሣኤው (26፥1—28፥20)
ምዕራፍ
Đang chọn:
የማቴዎስ ወንጌል መግቢያ: መቅካእኤ
Tô màu
Chia sẻ
Sao chép
Bạn muốn lưu những tô màu trên tất cả các thiết bị của mình? Đăng ký hoặc đăng nhập