1
ኦሪት ዘፀአት 15:26
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።
موازنہ
تلاش ኦሪት ዘፀአት 15:26
2
ኦሪት ዘፀአት 15:2
ጌታ ኃይሌና መዝሙሬ ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነዋለሁም፥ የአባቴ አምላክ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
تلاش ኦሪት ዘፀአት 15:2
3
ኦሪት ዘፀአት 15:11
ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
تلاش ኦሪት ዘፀአት 15:11
4
ኦሪት ዘፀአት 15:13
በታማኝ ኪዳንህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራሃቸው፤ በኃይልህ ወደ ቅድስናህ ማደሪያ አስገባሃቸው።
تلاش ኦሪት ዘፀአት 15:13
5
ኦሪት ዘፀአት 15:23-25
ወደ ማራም መጡ፥ የማራንም ውኃ ሊጠጡ አልቻሉም መራራ ነበረና፤ ስለዚህ አንድ ሰው ማራ ብሎ ጠራው። ሕዝቡም፦ “ምን እንጠጣለን?” ብለው በሙሴ ላይ አጉረመረሙ። እርሱም ወደ ጌታ ጮኸ፤ ጌታም ዛፍ አሳየው፥ በውኃውም ላይ ጣለው፥ ውኃውም ጣፋጭ ሆነ። ጌታም በዚያ ሥርዓትንና ፍርድን አደረገላቸው፥ በዚያም ፈተናቸው፤
تلاش ኦሪት ዘፀአት 15:23-25
صفحہ اول
بائبل
مطالعاتی منصوبہ
Videos