1
ማርቆስ 10:45
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
የሰው ልጅ እንዲያገለግሉት ሳይሆን፣ ለማገልገልና ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ለመስጠት መጥቷልና።”
موازنہ
تلاش ማርቆስ 10:45
2
ማርቆስ 10:27
ኢየሱስም አያቸውና፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉም ነገር ይቻላል” አላቸው።
تلاش ማርቆስ 10:27
3
ማርቆስ 10:52
ኢየሱስም፣ “ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” አለው፤ ወዲያውም ዐይኑ በራለት፤ በመንገድም ኢየሱስን ተከትሎት ሄደ።
تلاش ማርቆስ 10:52
4
ማርቆስ 10:9
ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው።”
تلاش ማርቆስ 10:9
5
ማርቆስ 10:21
ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ “እንግዲያው አንድ ነገር ይጐድልሃል፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድኾች ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ይኖርሃል፤ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው።
تلاش ማርቆስ 10:21
6
ማርቆስ 10:51
ኢየሱስም፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው። ዐይነ ስውሩም፣ “መምህር ሆይ፤ ዳግም እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው።
تلاش ማርቆስ 10:51
7
ማርቆስ 10:43
በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋይ ይሁን፤
تلاش ማርቆስ 10:43
8
ማርቆስ 10:15
እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበል ሁሉ ከቶ አይገባባትም።”
تلاش ማርቆስ 10:15
9
ማርቆስ 10:31
ነገር ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች፣ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።”
تلاش ማርቆስ 10:31
10
ማርቆስ 10:6-8
ነገር ግን በፍጥረት መጀመሪያ እግዚአብሔር ‘ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።’ ‘ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።’ ከእንግዲህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም።
تلاش ማርቆስ 10:6-8