1
ወደ ሮም ሰዎች 12:2
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Муқоиса
ወደ ሮም ሰዎች 12:2 омӯзед
2
ወደ ሮም ሰዎች 12:1
እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 12:1 омӯзед
3
ወደ ሮም ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:12 омӯзед
4
ወደ ሮም ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:21 омӯзед
5
ወደ ሮም ሰዎች 12:10
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:10 омӯзед
6
ወደ ሮም ሰዎች 12:9
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:9 омӯзед
7
ወደ ሮም ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:18 омӯзед
8
ወደ ሮም ሰዎች 12:19
ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
ወደ ሮም ሰዎች 12:19 омӯзед
9
ወደ ሮም ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:11 омӯзед
10
ወደ ሮም ሰዎች 12:3
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:3 омӯзед
11
ወደ ሮም ሰዎች 12:17
ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:17 омӯзед
12
ወደ ሮም ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:16 омӯзед
13
ወደ ሮም ሰዎች 12:20
ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
ወደ ሮም ሰዎች 12:20 омӯзед
14
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15 омӯзед
15
ወደ ሮም ሰዎች 12:13
ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:13 омӯзед
16
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5 омӯзед
Асосӣ
Китоби Муқаддас
Нақшаҳо
Видео