1
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እግዚአብሔርም አለ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁ፤ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰዉን በመልኩ ፈጠረ በእግአብሔር መልክ ፈጠራቸዉ።
Муқоиса
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27 омӯзед
2
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
እግዚአብሔርም ባረካቸዉ፤ እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትም ሁሉ ግዙአቸዉ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28 омӯзед
3
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ስማይንና ምድርን ፈጠረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1 омӯзед
4
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
ምድርም ባዶ ነበረች፤ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ስፍፎ ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2 омӯзед
5
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
እግዚአብሔርም፤ ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3 омӯзед
6
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
እግዚእብሔርም ያደረገዉን ሁሉ አየ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ስድስተኚ ቀን።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31 омӯзед
7
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4 омӯзед
8
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለዉን ሐመለማል ሁሉ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራዉንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29 омӯзед
9
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራዉ። ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አንድ ቀን።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5 омӯзед
10
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
እግዚአብሔርም፤ በዉኖች መካከል ጠፈር ይሁን በዉኂ መካከል ይከፈል አለ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6 омӯзед
11
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
ለምድርም አራዊት ሁሉ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ሕያዉ ነፍስ ላላቸዉ ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸዉ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30 омӯзед
12
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
እግዚአብሔርም አለ፤ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14 омӯзед
13
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
እግዚአብሔርም፤ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11 омӯзед
14
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኖች ለየ፤ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7 омӯзед
15
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12 омӯзед
16
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ከዋክብትም ደግሞ አደረገ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16 омӯзед
17
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
እግዚአብሔርም፤ ከሰማይ በታች ያለዉ ውኂ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራዉ የዉኂ መከማቻዉንም ባሕር አለዉ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10 омӯзед
18
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
እግዚእብሔርም እንድህ ብሎ ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኂ ሙሉአት ውፎችም በምድር ላይ ይብዙ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22 омӯзед
19
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24 омӯзед
20
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ፤ ዉኂ ሕያዉ ነፍስ ያላቸዉን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20 омӯзед
21
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25 омӯзед
Асосӣ
Китоби Муқаддас
Нақшаҳо
Видео