1
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
እግዚአብሔር የሚወዱትን ምርጦቹን በበጎ ምግባር ሁሉ እንደሚረዳቸው እናውቃለን።
Муқоиса
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28 омӯзед
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
ነገር ግን ሞትም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ አለቆችም ቢሆኑ፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንደማይችል አምናለሁ። ኀይልም ቢሆን፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል የለም።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39 омӯзед
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
መንፈስ ቅዱስም ከድካማችን ይረዳናል፤ እንግዲያስ ተስፋችንን ካላወቅን ጸሎታችን ምንድነው? ነገር ግን እርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ስለ መከራችንና ስለ ችግራችን ይፈርድልናል።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26 омӯзед
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለዚህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይችለናል?
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31 омӯзед
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
እንግዲህ በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉት በመንፈስ እንጂ በሥጋ ለማይመላለሱ ፍርድ የለባቸውም።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1 омӯзед
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
የሥጋ ዐሳብ ሞትን ያመጣብናል፤ የመንፈስ ዐሳብ ግን ሰላምንና ሕይወትን ይሰጠናል።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6 омӯзед
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
ነገር ግን በወደደን በእርሱ ሁሉን ድል እንነሣለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37 омӯзед
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
ነገር ግን የዚህ ዓለም መከራ ለእና ሊገለጥ ከአለው ክብር ጋር እንደማይተካከል ዐስቡ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18 омӯзед
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ነውን? ኀዘን ነውን? ስደት ነውን? ራብ ነውን? መራቆት ነውን? ጭንቀት ነውን? ሾተል ነውን?
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35 омӯзед
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
እርሱም ልባችንን ይመረምራል፤ ልብ የሚያስበውንም እርሱ ያውቃል፤ ስለ ቅዱሳንም በእግዚአብሔር ዘንድ ይፈርዳል።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27 омӯзед
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚሠሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14 омӯзед
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5 омӯзед
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
ለልጁ ስንኳ አልራራም፤ ስለ ሁላችን ቤዛ አድርጎ አሳልፎ ሰጠው እንጂ፥ እንግዲህ እርሱ ሁሉን እንዴት አይሰጠንም?
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32 омӯзед
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
እና የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆን ለልቡናችን ምስክሩ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው። እና የእግዚአብሔር ልጆች ከሆን ወራሾቹ ነን፤ የእግዚአብሔር ወራሾች ከሆንም የክርስቶስ ወራሾቹ ነን፤ በመከራ ከመሰልነውም በክብር እንመስለዋለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17 омӯзед
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
የሥጋ ዐሳብ ለእግዚአብሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእግዚአብሔርም ሕግ ስለማይገዛ፥ መፈጸም አይቻለውም።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7 омӯзед
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
የዓለም ተስፋው የእግዚአብሔርን ልጅ መምጣት ይጠባበቅ ነበርና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19 омӯзед
17
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
እስካሁን ዓለም ሁሉ ያዘነና የተከዘ እንደ ሆነ እናውቃለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22 омӯзед
Асосӣ
Китоби Муқаддас
Нақшаҳо
Видео