1
ኦሪት ዘፀአት 8:18-19
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
የግብፅ ጠንቋዮችም በአስማታቸው ቅማል ያወጡ ዘንድ እንዲሁ አደረጉ፤ ነገር ግን አልቻሉም፤ ቅማሉም በሰውና በእንስሳ ላይ ነበረ። ጠንቋዮችም ፈርዖንን፥ “ይህስ የእግዚአብሔር ጣት ነው” አሉት፤ የፈርዖን ልብ ግን ጸና፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።
Муқоиса
ኦሪት ዘፀአት 8:18-19 омӯзед
2
ኦሪት ዘፀአት 8:1
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
ኦሪት ዘፀአት 8:1 омӯзед
3
ኦሪት ዘፀአት 8:15
ፈርዖንም ጸጥታ እንደ ሆነ በአየ ጊዜ ልቡ ደነደነ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው አልሰማቸውም።
ኦሪት ዘፀአት 8:15 омӯзед
4
ኦሪት ዘፀአት 8:2
ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ ሀገርህን ሁሉ በጓጕንቸሮች እመታለሁ፤
ኦሪት ዘፀአት 8:2 омӯзед
5
ኦሪት ዘፀአት 8:16
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፦ ‘በትርህን በእጅህ ዘርጋ፤ የምድሩንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማልም በግብፅ ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ይወጣል።”
ኦሪት ዘፀአት 8:16 омӯзед
6
ኦሪት ዘፀአት 8:24
እግዚአብሔርም እንዲህ አደረገ፤ የውሻው ዝንብም በፈርዖን ቤት፥ በሹሞቹም ቤቶች ውሰጥ፥ በግብፅም ሀገር ሁሉ መጣ፤ ምድሪቱም ከውሻው ዝንብ የተነሣ ጠፋች።
ኦሪት ዘፀአት 8:24 омӯзед
Асосӣ
Китоби Муқаддас
Нақшаҳо
Видео