የሐዋርያት ሥራ 8:29-31
የሐዋርያት ሥራ 8:29-31 አማ2000
መንፈስ ቅዱስም ፊልጶስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረገላ ተከተለው” አለው። ፊልጶስም ፈጥኖ ደርሶ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማው፤ ፊልጶስም፥ “በውኑ የምታነበውን ታውቀዋለህን?” አለው። ጃንደረባውም፥ “ያስተማረኝ ሳይኖር በምን አውቀዋለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረገላውም ወጥቶ አብሮት ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።