1
ወደ ሮም ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Uporedi
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:28
2
ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
3
ወደ ሮም ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:26
4
ወደ ሮም ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:31
5
ወደ ሮም ሰዎች 8:1
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:1
6
ወደ ሮም ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:6
7
ወደ ሮም ሰዎች 8:37
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:37
8
ወደ ሮም ሰዎች 8:18
ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:18
9
ወደ ሮም ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:35
10
ወደ ሮም ሰዎች 8:27
ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:27
11
ወደ ሮም ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:14
12
ወደ ሮም ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:5
13
ወደ ሮም ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:32
14
ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከብር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
15
ወደ ሮም ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:7
16
ወደ ሮም ሰዎች 8:19
የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:19
17
ወደ ሮም ሰዎች 8:22
ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
Istraži ወደ ሮም ሰዎች 8:22
Početna
Biblija
Planovi
Video zapisi