1
የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
Uporedi
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
2
የማቴዎስ ወንጌል 5:14
እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 5:8
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:8
4
የማቴዎስ ወንጌል 5:6
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 5:44-45
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:44-45
6
የማቴዎስ ወንጌል 5:3
በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:3
7
የማቴዎስ ወንጌል 5:9
የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:9
8
የማቴዎስ ወንጌል 5:4
የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 5:10
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:10
10
የማቴዎስ ወንጌል 5:7
የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:7
11
የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
12
የማቴዎስ ወንጌል 5:5
የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:5
13
የማቴዎስ ወንጌል 5:13
እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:13
14
የማቴዎስ ወንጌል 5:48
እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:48
15
የማቴዎስ ወንጌል 5:37
ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:37
16
የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
17
የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
Početna
Biblija
Planovi
Video zapisi