1
የማቴዎስ ወንጌል 14:30-31
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ነገር ግን የነፋሱን ኀይል አይቶ ፈራ፤ ወደ ባሕሩ ውስጥ መስጠም በጀመረ ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ!” ሲል ጮኸ። ኢየሱስ ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ “አንተ እምነት የጐደለህ! ስለምን ተጠራጠርክ?” አለው።
Uporedi
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 14:30-31
2
የማቴዎስ ወንጌል 14:30
ነገር ግን የነፋሱን ኀይል አይቶ ፈራ፤ ወደ ባሕሩ ውስጥ መስጠም በጀመረ ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ!” ሲል ጮኸ።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 14:30
3
የማቴዎስ ወንጌል 14:27
ኢየሱስም ወዲያውኑ “አይዞአችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩ!” አላቸው።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 14:27
4
የማቴዎስ ወንጌል 14:28-29
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ፥ “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንክ በባሕሩ ላይ እየተራመድኩ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ!” አለው። ኢየሱስም “ና!” አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወርዶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ በባሕሩ ላይ ተራመደ።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 14:28-29
5
የማቴዎስ ወንጌል 14:33
በጀልባውም ውስጥ የነበሩት ሁሉ “በእርግጥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” ብለው ለኢየሱስ ሰገዱለት።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 14:33
6
የማቴዎስ ወንጌል 14:16-17
ኢየሱስ ግን፦ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው እንጂ እነርሱ እንዲሁ ሊሄዱ አይገባም!” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም “እኛ እዚህ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው” አሉት።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 14:16-17
7
የማቴዎስ ወንጌል 14:18-19
ኢየሱስም “እነርሱኑ ወደ እኔ አምጡልኝ!” አላቸው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ በመስኩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ አንሥቶ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና የምስጋና ጸሎት አደረገ፤ እንጀራውንም ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ዐደሉ።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 14:18-19
8
የማቴዎስ ወንጌል 14:20
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውን ፍርፋሪ፥ ደቀ መዛሙርቱ በዐሥራ ሁለት መሶብ ሞልተው አነሡ።
Istraži የማቴዎስ ወንጌል 14:20
Početna
Biblija
Planovi
Video zapisi