1
የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
Krahaso
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
2
የማቴዎስ ወንጌል 24:14
ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 24:6
ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:6
4
የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
5
የማቴዎስ ወንጌል 24:35
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:35
6
የማቴዎስ ወንጌል 24:5
ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:5
7
የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
8
የማቴዎስ ወንጌል 24:4
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 24:44
ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:44
10
የማቴዎስ ወንጌል 24:42
ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:42
11
የማቴዎስ ወንጌል 24:36
ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:36
12
የማቴዎስ ወንጌል 24:24
ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
Eksploroni የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
Kreu
Bibla
Plane
Video