1
የሉቃስ ወንጌል 6:38
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ስጡ፥ ይሰጣችኋልም፤ የሞላና የበዛ፥ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በዕቅፋችሁ ይሰጡአችኋል፤ በሰፈራችሁበትም መስፈሪያ ይሰፍሩላችኋል።”
සසඳන්න
የሉቃስ ወንጌል 6:38 ගවේෂණය කරන්න
2
የሉቃስ ወንጌል 6:45
መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካምን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል፤ ከልብ የተረፈውን አፍ ይናገራልና።
የሉቃስ ወንጌል 6:45 ගවේෂණය කරන්න
3
የሉቃስ ወንጌል 6:35
አሁንም ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉላቸው፤ እንዲመልሱላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ብዙ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለበጎዎችና ለክፉዎች ቸር ነውና።
የሉቃስ ወንጌል 6:35 ගවේෂණය කරන්න
4
የሉቃስ ወንጌል 6:36
ሰማያዊ አባታችሁ የሚራራ እንደ ሆነ እናንተም የምትራሩ ሁኑ።
የሉቃስ ወንጌል 6:36 ගවේෂණය කරන්න
5
የሉቃስ ወንጌል 6:37
አትፍረዱ፥ አይፈረድባችሁምም፤ አትበድሉ፥ አይበድሉአችሁምም፤ ይቅር በሉ፥ ይቅርም ይሉአችኋል።
የሉቃስ ወንጌል 6:37 ගවේෂණය කරන්න
6
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28
“ለምትሰሙኝ ለእናንተ ግን እንዲህ እላችኋለሁ፦ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ። የሚረግሙአችሁን መርቁአቸው፤ ለሚበድሉአችሁም ጸልዩላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28 ගවේෂණය කරන්න
7
የሉቃስ ወንጌል 6:31
ሰዎች ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱትም እንዲሁ እናንተ አድርጉላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 6:31 ගවේෂණය කරන්න
8
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30
ጕንጭህን ለሚመታህም ሁለተኛይቱን ስጠው፤ መጐናጸፊያህን ለሚወስድም ቀሚስህን ደግሞ አትከልክለው። ለሚለምንህም ሁሉ ስጥ፤ ገንዘብህን የሚወስደውንም እንዲመልስ አትጠይቀው።
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30 ගවේෂණය කරන්න
9
የሉቃስ ወንጌል 6:43
ክፉ ፍሬን የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለም፤ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ክፉ ዛፍም የለም።
የሉቃስ ወንጌል 6:43 ගවේෂණය කරන්න
10
የሉቃስ ወንጌል 6:44
ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃል፤ ከእሾህ በለስን አይለቅሙም፤ ከደንደርም ወይንን አይለቅሙም።
የሉቃስ ወንጌል 6:44 ගවේෂණය කරන්න
නිවස
බයිබලය
සැලසුම්
වීඩියෝ