1
የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
መብራትን አብርተው በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል እንጂ ከዕንቅብ በታች አያኖሩትም፤ በቤትም ላሉት ሁሉ ያበራል። መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ እንግዲህ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።
Comparar
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
2
የማቴዎስ ወንጌል 5:14
እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 5:8
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:8
4
የማቴዎስ ወንጌል 5:6
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ይጠግባሉና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 5:44
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:44
6
የማቴዎስ ወንጌል 5:3
በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:3
7
የማቴዎስ ወንጌል 5:9
ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:9
8
የማቴዎስ ወንጌል 5:4
የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መፅናናትን ያገኛሉና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 5:10
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:10
10
የማቴዎስ ወንጌል 5:7
ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:7
11
የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
“ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
12
የማቴዎስ ወንጌል 5:5
የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:5
13
የማቴዎስ ወንጌል 5:13
እናንተ የምድሪቱ ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ግን በምን ይጣፍጣል? በሰው ለመረገጥ ወደ ውጭ ከመጣል በስተቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:13
14
የማቴዎስ ወንጌል 5:48
ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:48
15
የማቴዎስ ወንጌል 5:37
ስለዚህ ንግግራችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከእነዚህ የተረፈ ግን ከክፉው ነው።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:37
16
የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
“‘ዐይን ስለ ዐይን፥ ጥርስ ስለ ጥርስ’ እንደተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ክፉውን አትቃወሙት፤ ነገር ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
17
የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
ቀኝ ዐይንህ ብታሰናክልህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱ ክፍል ቢጠፋ ይሻልሃልና። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ከአንተ ቆርጠህ ጣላት፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱ ክፍል ቢጠፋ ይሻልሃልና።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
Início
Bíblia
Planos
Vídeos