1
የሉቃስ ወንጌል 6:38
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።
Compare
የሉቃስ ወንጌል 6:38ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የሉቃስ ወንጌል 6:45
በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል።
የሉቃስ ወንጌል 6:45ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የሉቃስ ወንጌል 6:35
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ምንም ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፥ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፥ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፥ እርሱ ለማያመሰግኑ ለክፉዎችም ቸር ነውና።
የሉቃስ ወንጌል 6:35ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የሉቃስ ወንጌል 6:36
አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።
የሉቃስ ወንጌል 6:36ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የሉቃስ ወንጌል 6:37
አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።
የሉቃስ ወንጌል 6:37ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28
ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፥ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ።
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የሉቃስ ወንጌል 6:31
ሰዎችም ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 6:31ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30
ጕንጭህን ለሚመታህ ደግሞ ሁለተኛውን ስጠው፥ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን ደግሞ አትከልክለው። ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፥ ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
የሉቃስ ወንጌል 6:43
ክፉ ፍሬ የሚያደርግ መልካም ዛፍ የለምና፥ እንዲሁም መልካም ፍሬ የሚያደርግ ክፉ ዛፍ የለም።
የሉቃስ ወንጌል 6:43ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
የሉቃስ ወንጌል 6:44
ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃልና፤ ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፥ ከአጣጥ ቍጥቋጦም ወይን አይቈርጡም።
የሉቃስ ወንጌል 6:44ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ