1
ወደ ሮም ሰዎች 12:2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
መልካሙንና ደስ የሚያሰኘውን ፍጹም የሆነውንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮአችሁን በማደስ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉት።
Compare
ወደ ሮም ሰዎች 12:2ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
ወደ ሮም ሰዎች 12:1
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 12:1ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
ወደ ሮም ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ታገሡ፤ ሁልጊዜ ጸልዩ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:12ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
ወደ ሮም ሰዎች 12:21
ስለዚህ ክፉውን ነገር በመልካም ነገር አሸንፍ እንጂ በክፉ ነገር አትሸነፍ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:21ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
ወደ ሮም ሰዎች 12:10
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ለመከባበርም ተሽቀዳደሙ፤
ወደ ሮም ሰዎች 12:10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
ወደ ሮም ሰዎች 12:9
ግብዝነት የሌለበት እውነተኛ ፍቅር ይኑራችሁ፤ ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካሙን ነገር ተከተሉ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:9ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
ወደ ሮም ሰዎች 12:18
የሚቻላችሁ ቢሆን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጉ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:18ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
ወደ ሮም ሰዎች 12:19
ወዳጆቼ ሆይ! ቊጣን ለእግዚአብሔር ተዉ እንጂ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “የምበቀልና የበቀልንም ብድራት የምከፍል እኔ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአል።
ወደ ሮም ሰዎች 12:19ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
ወደ ሮም ሰዎች 12:11
ሳትታክቱ የጋለ መንፈስን ተከትላችሁ ጌታን አገልግሉ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
ወደ ሮም ሰዎች 12:3
ደግሞም እያንዳንዳችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ እምነት መጠን በትሕትና አስቡ እንጂ ከሚገባችሁ በላይ ስለ ራሳችሁ በትዕቢት አታስቡ ብዬ በተሰጠኝ ጸጋ እነግራችኋለሁ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:3ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
ወደ ሮም ሰዎች 12:17
በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አድርጉ እንጂ፥ ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርጉባችሁ፥ እናንተም መልሳችሁ ክፉ ነገር አታድርጉባቸው።
ወደ ሮም ሰዎች 12:17ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
12
ወደ ሮም ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:16ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
13
ወደ ሮም ሰዎች 12:20
ስለዚህ ከመበቀል ይልቅ ጠላትህን ቢርበው አብላው፤ ቢጠማውም አጠጣው፤ ይህን ብታደርግ በዕፍረት እሳት ታቃጥለዋለህ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:20ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
14
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁንም መርቁ፤ መርቁአቸው እንጂ አትርገሙአቸው። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
15
ወደ ሮም ሰዎች 12:13
አማኞች ወንድሞችን በችግራቸው እርዱ፤ በእንግድነት የሚመጡትንም ተቀበሉ።
ወደ ሮም ሰዎች 12:13ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
16
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
በአንዱ አካላችን ብዙ ክፍሎች አሉ፤ እያንዳንዱም የአካል ክፍል የተለየ ሥራ አለው። እንዲሁም እኛ ብዙዎች ሆነን ሳለ በክርስቶስ አንድ አካል ነን፤ የአንድ አካል ክፍሎች እንደ መሆናችንም እርስ በርሳችን ተጣምረናል።
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ