1
የሉቃስ ወንጌል 17:19
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው፦ “ተነሥና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።
Compare
የሉቃስ ወንጌል 17:19ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የሉቃስ ወንጌል 17:4
በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህና በቀን ሰባት ጊዜም ወደ አንተ እየመጣ ‘በበደሌ ተጸጽቼአለሁ’ ቢልህ ይቅር በለው።”
የሉቃስ ወንጌል 17:4ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የሉቃስ ወንጌል 17:15-16
ከእነርሱም አንዱ ከለምጹ መንጻቱን ባየ ጊዜ በከፍተኛ ድምፅ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ተመለሰ። ኢየሱስንም እያመሰገነ በእግሩ ሥር በግምባሩ ተደፋ፤ እርሱ የሰማርያ ሰው ነበር።
የሉቃስ ወንጌል 17:15-16ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የሉቃስ ወንጌል 17:3
ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ! ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው! በበደሉ ከተጸጸተም ይቅር በለው!
የሉቃስ ወንጌል 17:3ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የሉቃስ ወንጌል 17:17
ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “ከለምጽ የነጹት ሰዎች ዐሥር አልነበሩምን? ታዲያ፥ ዘጠኙ የት አሉ?
የሉቃስ ወንጌል 17:17ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የሉቃስ ወንጌል 17:6
ጌታ ኢየሱስም “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ በባሕር ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዝላችኋል” አላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 17:6ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የሉቃስ ወንጌል 17:33
ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ያድናታል።
የሉቃስ ወንጌል 17:33ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
የሉቃስ ወንጌል 17:1-2
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “ሰዎችን አሰናክለው ወደ ኃጢአት የሚጥሉ ነገሮች መምጣታቸው አይቀርም፤ ነገር ግን የኃጢአትን መሰናክል ለሚያመጣው ለዚያ ሰው ወዮለት! ማንም ሰው ከእነዚህ ታናናሾች አንዱን ከሚያሰናክል ይልቅ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር።
የሉቃስ ወንጌል 17:1-2ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
የሉቃስ ወንጌል 17:26-27
በኖኅ ዘመን እንደሆነው ዐይነት የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜም እንዲሁ ይሆናል። ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፥ ሲያገቡና ሲጋቡም ነበር፤ በዚያን ጊዜ የጥፋት ውሃ መጣና አጥለቅልቆ ሁሉንም አጠፋቸው።
የሉቃስ ወንጌል 17:26-27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ