1
የሉቃስ ወንጌል 14:26
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
Compare
የሉቃስ ወንጌል 14:26ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የሉቃስ ወንጌል 14:27
የራሱን መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ፥ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
የሉቃስ ወንጌል 14:27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የሉቃስ ወንጌል 14:11
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ግን ከፍ ይላል።”
የሉቃስ ወንጌል 14:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የሉቃስ ወንጌል 14:33
እንዲሁም ከእናንተ መካከል ያለውን ሁሉ ለእኔ ሲል ያልተወ ማንም ሰው የእኔ ደቀ መዝሙር መሆን አይችልም።”
የሉቃስ ወንጌል 14:33ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30
“ከእናንተ መካከል አንዱ ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለሥራው ማስፈጸሚያ ምን ያኽል ገንዘብ እንደሚያስፈልገው አስቀድሞ የማያስብ ማነው? መሠረቱን ጥሎ የሕንጻውን ሥራ መፈጸም ያልቻለ እንደ ሆነ ግን በጅምር የቀረውን ቤት የሚያዩት ሁሉ ይዘባበቱበታል፤ ‘እነሆ፥ ይህ ሰው ቤት መሥራት ጀምሮ መጨረስ አልቻለም’ እያሉ ያፌዙበታል።
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14
ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድኾችን፥ አካለ ስንኩሎችን፥ ሽባዎችን፥ ዕውሮችንም ሰዎች ጥራ። ይህን ብታደርግ እነርሱ ውለታ ለመክፈል ስለማይችሉ የተባረክህ ትሆናለህ። በጻድቃን ትንሣኤ ጊዜም እግዚአብሔር ይከፍልሃል።”
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ጨው መልካም ነው፤ ጨው የጨውነቱን ጣዕም ካጣ ግን በምን ሊጣፍጥ ይችላል? እንዲህ ዐይነቱ ጨው ለእርሻ መሬትም ሆነ ለማዳበሪያ የማይጠቅም ስለ ሆነ ወዲያ አውጥተው ይጥሉታል፤ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ