1
የዮሐንስ ወንጌል 6:35
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ፈጽሞ አይራብም፤ በእኔ የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም፤
Compare
የዮሐንስ ወንጌል 6:35ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የዮሐንስ ወንጌል 6:63
ሕይወትን የሚሰጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሰው ኀይል ግን ለምንም አይጠቅምም፤ እኔ ለእናንተ የተናገርኩት ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው፤
የዮሐንስ ወንጌል 6:63ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የዮሐንስ ወንጌል 6:27
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
የዮሐንስ ወንጌል 6:27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የዮሐንስ ወንጌል 6:40
አዎ! የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያይና በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።”
የዮሐንስ ወንጌል 6:40ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የዮሐንስ ወንጌል 6:29
ኢየሱስም “የእግዚአብሔር ሥራማ እግዚአብሔር በላከው ማመን ነው” ሲል መለሰላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 6:29ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የዮሐንስ ወንጌል 6:37
አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ፈጽሞ ወደ ውጪ አላባርረውም።
የዮሐንስ ወንጌል 6:37ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የዮሐንስ ወንጌል 6:68
በዚህ ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ።
የዮሐንስ ወንጌል 6:68ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
የዮሐንስ ወንጌል 6:51
ከሰማይ የወረደው ሕይወትን የሚሰጥ እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ሁሉ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን እኔ የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።”
የዮሐንስ ወንጌል 6:51ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
የዮሐንስ ወንጌል 6:44
የላከኝ አብ የሳበው ካልሆነ በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል ማንም የለም፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም በመጨረሻ ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 6:44ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
የዮሐንስ ወንጌል 6:33
የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድና ለዓለም ሕይወትን የሚሰጥ ነው።”
የዮሐንስ ወንጌል 6:33ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
የዮሐንስ ወንጌል 6:48
እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ፤
የዮሐንስ ወንጌል 6:48ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
12
የዮሐንስ ወንጌል 6:11-12
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንጀራውን አንሥቶ ምስጋና ካቀረበ በኋላ ለተቀመጡት ሰዎች ዐደላቸው። እንዲሁም ዓሣዎቹን አከፋፈላቸው፤ ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ያኽል አገኙ። ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “አንድም ነገር እንዳይባክን የተረፈውንም ፍርፋሪ ሰብስቡ” አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 6:11-12ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
13
የዮሐንስ ወንጌል 6:19-20
ደቀ መዛሙርቱ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያኽል እየቀዘፉ ከተጓዙ በኋላ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቀርብ አይተው ፈሩ። እርሱ ግን “እኔ ነኝ! አትፍሩ!” አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 6:19-20ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ