1
ኦሪት ዘፍጥረት 35:11-12
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑርህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ። ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠሁትን ምድር ለአንተም እሰጥሃለሁ፤ ይህንኑ ምድር ከአንተም በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ።”
Compare
ኦሪት ዘፍጥረት 35:11-12ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
ኦሪት ዘፍጥረት 35:3
ከዚህ ተነሥተን ወደ ቤትኤል እንውጣ፤ በዚያም ከዚህ በፊት በተቸገርኩ ጊዜ ጸሎቴን ሰምቶ ለረዳኝና በሄድኩበት ስፍራ ሁሉ ከእኔ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 35:3ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
ኦሪት ዘፍጥረት 35:10
ደግሞም “ስምህ ያዕቆብ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን እስራኤል ትባላለህ እንጂ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም” አለው። ስለዚህም እግዚአብሔር ያዕቆብን “እስራኤል” ብሎ ጠራው።
ኦሪት ዘፍጥረት 35:10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
ኦሪት ዘፍጥረት 35:2
ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ንጹሕ ልብስም ልበሱ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 35:2ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
ኦሪት ዘፍጥረት 35:1
እግዚአብሔር ያዕቆብን “አሁን ተነሥተህ ወደ ቤትኤል ሂድና እዚያ ኑር፤ በዚያም ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድክ ጊዜ ለተገለጥኩልህ አምላክ ለእኔ መሠዊያ ሥራ” አለው።
ኦሪት ዘፍጥረት 35:1ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
ኦሪት ዘፍጥረት 35:18
እርስዋ ግን ልትሞት ታጣጥር ስለ ነበር ከመሞቷ በፊት ልጅዋን “ቤንኦኒ” አለችው፤ አባቱ ግን “ብንያም” አለው።
ኦሪት ዘፍጥረት 35:18ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ