1
ኦሪት ዘጸአት 20:2-3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በባርነት ከምትኖርባት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ፤
Compare
ኦሪት ዘጸአት 20:2-3ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
ኦሪት ዘጸአት 20:4-5
“በሰማይም ሆነ በምድር ወይም ከምድር በታች ባለው ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ነገሮች የማንኛውንም ዐይነት ምስል ጣዖት አድርገህ አትሥራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
ኦሪት ዘጸአት 20:4-5ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
ኦሪት ዘጸአት 20:12
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።
ኦሪት ዘጸአት 20:12ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
ኦሪት ዘጸአት 20:8
“የሰንበትን ቀን አክብር፤ ቀድሰውም፤
ኦሪት ዘጸአት 20:8ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
ኦሪት ዘጸአት 20:7
“የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሁሉ ሳይቀጣው አያልፍም።
ኦሪት ዘጸአት 20:7ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
ኦሪት ዘጸአት 20:9-10
ሥራህን ሁሉ የምታከናውንባቸው ስድስት ቀኖች አሉልህ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ማንም ሰው ሥራ አይሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ፥ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት።
ኦሪት ዘጸአት 20:9-10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
ኦሪት ዘጸአት 20:17
“የሌላውን ሰው ቤት አትመኝ፤ ሚስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።”
ኦሪት ዘጸአት 20:17ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
ኦሪት ዘጸአት 20:16
“በማንም ሰው ላይ በሐሰት አትመስክር፤
ኦሪት ዘጸአት 20:16ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
ኦሪት ዘጸአት 20:14
“አታመንዝር፤
ኦሪት ዘጸአት 20:14ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
ኦሪት ዘጸአት 20:13
“አትግደል፤
ኦሪት ዘጸአት 20:13ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
ኦሪት ዘጸአት 20:15
“አትስረቅ፤
ኦሪት ዘጸአት 20:15ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ