1
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
Compare
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:57
ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:57ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33
አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:10
ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:55-56
እንዲሁም፥ “ሞት ሆይ! ድል መንሣትህ የት ነው? ሞት ሆይ! ሰውን የምትጐዳበት ኀይል የት ነው?” ተብሎአል። የሞት መንደፊያ ኀይል ኃጢአት ነው፤ የኃጢአትም ኀይል ሕግ ነው።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:55-56ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51-52
እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ። እኛ ሁላችንም አንሞትም፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን። የምንለወጠውም የመጨረሻው እምቢልታ በሚነፋበት ጊዜ እንደ ዐይን ቅጽበት በአንድ ጊዜ ነው። መለከቱ ይነፋል፤ የሞቱትም ሰዎች የማይጠፉ ሕያዋን ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን፤
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51-52ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:21-22
ሞት የመጣው በአንዱ ሰው በአዳም ምክንያት እንደ ሆነ ከሞት መነሣትም የሚመጣው በአንዱ ሰው በክርስቶስ ምክንያት ነው። በአዳም ምክንያት ሰው ሁሉ እንደሚሞት እንዲሁም በክርስቶስ ምክንያት ሰው ሁሉ ሕይወትን ያገኛል።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:21-22ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:53
ይህ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይህም የሚሞተው የማይሞተውን መልበስ አለበት።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:53ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25-26
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ሁሉ በሥልጣኑ ሥር እስኪያደርግለት ድረስ ክርስቶስ መንገሥ ይገባዋል። ተሸንፎ በመጨረሻ የሚደመሰሰው ጠላት ሞት ነው።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25-26ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ