1
ኦሪት ዘፍጥረት 22:14
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አብርሃም ያንን ቦታ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ሰየመው፤ ዛሬም ቢሆን ሰዎች “እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል” ይላሉ።
ႏွိုင္းယွဥ္
ኦሪት ዘፍጥረት 22:14ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
2
ኦሪት ዘፍጥረት 22:2
እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው።
ኦሪት ዘፍጥረት 22:2ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
3
ኦሪት ዘፍጥረት 22:12
መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 22:12ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
4
ኦሪት ዘፍጥረት 22:8
አብርሃምም “ልጄ ሆይ፥ ለመሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ለራሱ ያዘጋጃል” አለው፤ ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።
ኦሪት ዘፍጥረት 22:8ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
5
ኦሪት ዘፍጥረት 22:17-18
እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነሥተው ከተሞቻቸውን ይይዛሉ። ትእዛዜን ስለ ፈጸምክ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 22:17-18ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
6
ኦሪት ዘፍጥረት 22:1
ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ።
ኦሪት ዘፍጥረት 22:1ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
7
ኦሪት ዘፍጥረት 22:11
ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ።
ኦሪት ዘፍጥረት 22:11ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
8
ኦሪት ዘፍጥረት 22:15-16
የእግዚአብሔር መልአክ ሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ጠራውና እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ‘ብዙ በረከት እንደምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ’ ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቈጠብክ፥
ኦሪት ዘፍጥረት 22:15-16ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
9
ኦሪት ዘፍጥረት 22:9
እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሠዊያው ላይ አጋደመው።
ኦሪት ዘፍጥረት 22:9ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
ပင္မစာမ်က္ႏွာ
သမၼာက်မ္းစာ
အစီအစဥ္မ်ား
ဗီဒီယိုမ်ား