1
የማቴዎስ ወንጌል 19:26
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ “ይህ ነገር ለሰው የማይቻል ነው፤ ለእግዚአብሔር ግን ሁሉም ይቻለዋል” አለ።
तुलना करा
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:26
2
የማቴዎስ ወንጌል 19:6
ስለዚህ እነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አንድ አካል ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። እንግዲህ እግዚአብሔር አጣምሮ አንድ ያደረገውን ሰው አይለየው።”
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:6
3
የማቴዎስ ወንጌል 19:4-5
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸው አላነበባችሁምን? ደግሞም ‘በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይዋሓዳል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ’
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:4-5
4
የማቴዎስ ወንጌል 19:14
ኢየሱስም፦ “መንግሥተ ሰማይ እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሉአቸው” አለ።
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:14
5
የማቴዎስ ወንጌል 19:30
ነገር ግን አሁን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች ይሆናሉ፤ ኋለኞች የሆኑትም ፊተኞች ይሆናሉ።”
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:30
6
የማቴዎስ ወንጌል 19:29
ስለ እኔ ብሎ ቤቶችን፥ ወይም ወንድሞችን፥ ወይም እኅቶችን፥ ወይም አባትን ወይም እናትን፥ ወይም ልጆችን፥ ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘለዓለም ሕይወትንም ያገኛል።
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:29
7
የማቴዎስ ወንጌል 19:21
ኢየሱስም “ፍጹም መሆን ብትፈልግ ሂድና ያለህን ሸጠህ ገንዘቡን ለድኻ ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ” አለው።
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:21
8
የማቴዎስ ወንጌል 19:17
ኢየሱስም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ግን ትእዛዞችን ፈጽም” አለው።
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:17
9
የማቴዎስ ወንጌል 19:24
ደግሞም እላችኋለሁ፦ ሀብታም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል።”
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:24
10
የማቴዎስ ወንጌል 19:9
“እኔ ግን፥ ‘አንድ ሰው በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሴት ቢያገባ አመነዘረ’ እላችኋለሁ።”
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:9
11
የማቴዎስ ወንጌል 19:23
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ለሀብታም ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ መግባት በጣም ከባድ ነው።
एक्सप्लोर करा የማቴዎስ ወንጌል 19:23
मुख्य
बायबल
योजना
व्हिडिओ