ትን​ቢተ ዮናስ 4:10-11

ትን​ቢተ ዮናስ 4:10-11 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አንተ ትበ​ቅል ዘንድ ላል​ደ​ከ​ም​ህ​ባት፥ ላላ​ሳ​ደ​ግ​ሃ​ትም፥ በአ​ንድ ሌሊት ለበ​ቀ​ለች፥ በአ​ንድ ሌሊ​ትም ለደ​ረ​ቀ​ችው ቅል አዝ​ነ​ሃል። እኔስ ቀኛ​ቸ​ው​ንና ግራ​ቸ​ውን የማ​ይ​ለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚ​በ​ልጡ ሰዎ​ችና ብዙ እን​ስ​ሶች ላሉ​ባት ለታ​ላ​ቂቱ ከተማ ለነ​ነዌ አላ​ዝ​ን​ምን?” አለው።