1
የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
비교
የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16 살펴보기
2
የማቴዎስ ወንጌል 5:14
እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
የማቴዎስ ወንጌል 5:14 살펴보기
3
የማቴዎስ ወንጌል 5:8
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:8 살펴보기
4
የማቴዎስ ወንጌል 5:6
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:6 살펴보기
5
የማቴዎስ ወንጌል 5:44-45
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:44-45 살펴보기
6
የማቴዎስ ወንጌል 5:3
በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:3 살펴보기
7
የማቴዎስ ወንጌል 5:9
የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:9 살펴보기
8
የማቴዎስ ወንጌል 5:4
የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:4 살펴보기
9
የማቴዎስ ወንጌል 5:10
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:10 살펴보기
10
የማቴዎስ ወንጌል 5:7
የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:7 살펴보기
11
የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12 살펴보기
12
የማቴዎስ ወንጌል 5:5
የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:5 살펴보기
13
የማቴዎስ ወንጌል 5:13
እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።
የማቴዎስ ወንጌል 5:13 살펴보기
14
የማቴዎስ ወንጌል 5:48
እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።
የማቴዎስ ወንጌል 5:48 살펴보기
15
የማቴዎስ ወንጌል 5:37
ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው።
የማቴዎስ ወንጌል 5:37 살펴보기
16
የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤
የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39 살펴보기
17
የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።
የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상