1
ኦሪት ዘፀአት 20:2-3
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
“ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ።
비교
ኦሪት ዘፀአት 20:2-3 살펴보기
2
ኦሪት ዘፀአት 20:4-5
“በላይ በሰማይ ከአለው፥ በታችም በምድር ከአለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ከአለው ነገር የማናቸውንም ምስል ለአንተ አምላክ አታድርግ። አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ኦሪት ዘፀአት 20:4-5 살펴보기
3
ኦሪት ዘፀአት 20:12
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
ኦሪት ዘፀአት 20:12 살펴보기
4
ኦሪት ዘፀአት 20:8
“የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አስብ።
ኦሪት ዘፀአት 20:8 살펴보기
5
ኦሪት ዘፀአት 20:7
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
ኦሪት ዘፀአት 20:7 살펴보기
6
ኦሪት ዘፀአት 20:9-10
ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ ሰባተኛዋ ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ አህያህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርስዋ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
ኦሪት ዘፀአት 20:9-10 살펴보기
7
ኦሪት ዘፀአት 20:17
“የባልንጀራህን ሚስት፥ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ እርሻውንም፥ ሎሌውንም፥ ገረዱንም፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከብቱንም ሁሉ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማንኛውንም አትመኝ።”
ኦሪት ዘፀአት 20:17 살펴보기
8
ኦሪት ዘፀአት 20:16
“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
ኦሪት ዘፀአት 20:16 살펴보기
9
ኦሪት ዘፀአት 20:14
“አታመንዝር።
ኦሪት ዘፀአት 20:14 살펴보기
10
ኦሪት ዘፀአት 20:13
“አትግደል።
ኦሪት ዘፀአት 20:13 살펴보기
11
ኦሪት ዘፀአት 20:15
“አትስረቅ።
ኦሪት ዘፀአት 20:15 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상