1
የሉቃስ ወንጌል 6:38
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ስጡ ይሰጣችኋልም፤ በመልካምም መስፈሪያ የተጠቀጠቀና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና።”
비교
የሉቃስ ወንጌል 6:38 살펴보기
2
የሉቃስ ወንጌል 6:45
መልካም ሰው በልቡ ከሚገኘው መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ከሚገኘው ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል፤ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና።
የሉቃስ ወንጌል 6:45 살펴보기
3
የሉቃስ ወንጌል 6:35
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉ፤ ይመለስልናልም ብላችሁ ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።
የሉቃስ ወንጌል 6:35 살펴보기
4
የሉቃስ ወንጌል 6:36
አባታችሁ ርኅሩኅ እንደሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።
የሉቃስ ወንጌል 6:36 살펴보기
5
የሉቃስ ወንጌል 6:37
“አትፍረዱ እንዳይፈረድባችሁም፤ አትኰንኑ እንዳትኰነኑም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ፤
የሉቃስ ወንጌል 6:37 살펴보기
6
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28
“ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ።
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28 살펴보기
7
የሉቃስ ወንጌል 6:31
እንዲሁም ሰዎች ለእናንተ እንዲያደርጉላችሁ የምትወድዱትን ነገር እናንተ ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 6:31 살펴보기
8
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30
ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጉንጭህን ደግሞ ስጠው፤ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን እንኳ አትከልክለው። ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤ ንብረትህንም የሚወስድብህን ሰው እንዲመልስ አትጠይቀው።
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30 살펴보기
9
የሉቃስ ወንጌል 6:43
መልካም ዛፍ የተበላሸ ፍሬ አያፈራምና፤ እንዲሁም የተበላሸ ዛፍ መልካም ፍሬ አያፈራም።
የሉቃስ ወንጌል 6:43 살펴보기
10
የሉቃስ ወንጌል 6:44
ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃልና፤ ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፤ ከአጣጥ ቁጥቋጦም ወይን አይቈርጡም።
የሉቃስ ወንጌል 6:44 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상