1
የዮሐንስ ወንጌል 14:27
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይታወክ፤ አይፍራም።
비교
የዮሐንስ ወንጌል 14:27 살펴보기
2
የዮሐንስ ወንጌል 14:6
ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።
የዮሐንስ ወንጌል 14:6 살펴보기
3
የዮሐንስ ወንጌል 14:1
“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።
የዮሐንስ ወንጌል 14:1 살펴보기
4
የዮሐንስ ወንጌል 14:26
አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 14:26 살펴보기
5
የዮሐንስ ወንጌል 14:21
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
የዮሐንስ ወንጌል 14:21 살펴보기
6
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
እኔም አብን እለምናለሁ፤ ለዘለዓለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ምክንያቱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ነው። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፥ በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17 살펴보기
7
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
አብ በወልድ እንዲከብር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14 살펴보기
8
የዮሐንስ ወንጌል 14:15
“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 14:15 살펴보기
9
የዮሐንስ ወንጌል 14:2
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ እላችሁ ነበርን?
የዮሐንስ ወንጌል 14:2 살펴보기
10
የዮሐንስ ወንጌል 14:3
ሄጄም ስፍራ ሳዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትኖሩ ዳግምኛ እመጣለሁ፤ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 14:3 살펴보기
11
የዮሐንስ ወንጌል 14:5
ቶማስም “ጌታ ሆይ! ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው።
የዮሐንስ ወንጌል 14:5 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상