1
ኦሪት ዘጸአት 20:2-3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በባርነት ከምትኖርባት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ፤
비교
ኦሪት ዘጸአት 20:2-3 살펴보기
2
ኦሪት ዘጸአት 20:4-5
“በሰማይም ሆነ በምድር ወይም ከምድር በታች ባለው ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ነገሮች የማንኛውንም ዐይነት ምስል ጣዖት አድርገህ አትሥራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
ኦሪት ዘጸአት 20:4-5 살펴보기
3
ኦሪት ዘጸአት 20:12
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።
ኦሪት ዘጸአት 20:12 살펴보기
4
ኦሪት ዘጸአት 20:8
“የሰንበትን ቀን አክብር፤ ቀድሰውም፤
ኦሪት ዘጸአት 20:8 살펴보기
5
ኦሪት ዘጸአት 20:7
“የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሁሉ ሳይቀጣው አያልፍም።
ኦሪት ዘጸአት 20:7 살펴보기
6
ኦሪት ዘጸአት 20:9-10
ሥራህን ሁሉ የምታከናውንባቸው ስድስት ቀኖች አሉልህ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ማንም ሰው ሥራ አይሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ፥ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት።
ኦሪት ዘጸአት 20:9-10 살펴보기
7
ኦሪት ዘጸአት 20:17
“የሌላውን ሰው ቤት አትመኝ፤ ሚስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።”
ኦሪት ዘጸአት 20:17 살펴보기
8
ኦሪት ዘጸአት 20:16
“በማንም ሰው ላይ በሐሰት አትመስክር፤
ኦሪት ዘጸአት 20:16 살펴보기
9
ኦሪት ዘጸአት 20:14
“አታመንዝር፤
ኦሪት ዘጸአት 20:14 살펴보기
10
ኦሪት ዘጸአት 20:13
“አትግደል፤
ኦሪት ዘጸአት 20:13 살펴보기
11
ኦሪት ዘጸአት 20:15
“አትስረቅ፤
ኦሪት ዘጸአት 20:15 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상