1
የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ሰዎች መብራት አብርተው በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በከፍተኛ ቦታ ያስቀምጡታል እንጂ ከእንቅብ በታች አያኖሩትም። እንዲሁም ሰዎች መልካም ሥራችሁን አይተው የሰማይ አባታችሁን እንዲያመሰግኑት፥ የእናንተም ብርሃን በሰው ፊት ይብራ።”
Bera saman
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
2
የማቴዎስ ወንጌል 5:14
እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ የተሠራች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 5:8
እግዚአብሔርን ስለሚያዩት ንጹሕ ልብ ያላቸው የተባረኩ ናቸው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:8
4
የማቴዎስ ወንጌል 5:6
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ስለሚጠግቡ የተባረኩ ናቸው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 5:44
እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁ በጎ አድርጉ፤ ክፉ ለሚያደርጉባችሁና ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” እላችኋለሁ።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:44
6
የማቴዎስ ወንጌል 5:3
“መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ስለ ሆነች በመንፈሳዊ ኑሮአቸው ድኾች መሆናቸው የሚሰማቸው የተባረኩ ናቸው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:3
7
የማቴዎስ ወንጌል 5:9
በሰዎች መካከል ዕርቅና ሰላምን የሚያደርጉ፥ የእግዚአብሔር ልጆች ስለሚባሉ የተባረኩ ናቸው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:9
8
የማቴዎስ ወንጌል 5:4
እግዚአብሔር መጽናናትን ስለሚሰጣቸው የሚያዝኑ የተባረኩ ናቸው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 5:10
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ፥ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ስለ ሆነች የተባረኩ ናቸው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:10
10
የማቴዎስ ወንጌል 5:7
ምሕረትን ስለሚያገኙ ምሕረትን የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:7
11
የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
“በእኔ ምክንያት ሰዎች ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ፥ በውሸትም ስማችሁን ሲያጠፉት ደስ ይበላችሁ። በመንግሥተ ሰማይ የምታገኙት ዋጋ ትልቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ። ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንዲሁ ስደትና መከራ አድርሰውባቸዋል።”
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
12
የማቴዎስ ወንጌል 5:5
ትሑቶች ምድርን ስለሚወርሱ የተባረኩ ናቸው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:5
13
የማቴዎስ ወንጌል 5:13
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እናንተ እንደ ምድር ጨው ናችሁ፤ ነገር ግን ጨው ጣዕሙን ካጣ እንዴት ጣዕሙን መልሶ ሊያገኝ ይችላል? ወደ ውጪ ከመጣልና በሰው እግር ከመረገጥ በቀር ወደፊት ለምንም አይጠቅምም።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:13
14
የማቴዎስ ወንጌል 5:48
ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹሞች ሁኑ።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:48
15
የማቴዎስ ወንጌል 5:37
ስለዚህ ንግግራችሁ “አዎ” ከሆነ “አዎ፥” ወይም “አይደለም” ከሆነ “አይደለም” ይሁን። ከዚህ የተረፈ ቃል ግን ከሰይጣን ነው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:37
16
የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
“ ‘ዐይን ስለ ዐይን፥ ጥርስ ስለ ጥርስ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ፤ ክፉ የሚያደርግባችሁን ሰው አትበቀሉት። ነገር ግን ቀኝ ጒንጭህን ለሚመታህ፥ ግራ ጒንጭህን አዙርለት።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
17
የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
የቀኝ ዐይንህ ለኃጢአት ምክንያት ቢሆንብህ፥ አውጥተህ ጣለው! ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል። ቀኝ እጅህ የኃጢአት ምክንያት ቢሆንብህ፥ ቈርጠህ ጣለው! ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
Heim
Biblía
Áætlanir
Myndbönd