1
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:17-18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። እንደዚህ አድርጎ ክርስቶስን የሚያገልግል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።
Lee anya n'etiti ihe abụọ
Nyochaa ወደ ሮሜ ሰዎች 14:17-18
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:8
በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።
Nyochaa ወደ ሮሜ ሰዎች 14:8
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:19
እንግዲህ የሰላም ነገርና እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን ነገር እንከተል።
Nyochaa ወደ ሮሜ ሰዎች 14:19
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:13
እንግዲህ ከዚህ በኋላ አንዳችን በአንዳችን ላይ አንፍረድ፤ ነገር ግን ከመፍረድ ይልቅ ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይወስን።
Nyochaa ወደ ሮሜ ሰዎች 14:13
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:11-12
“እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል ጌታ፤ “ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ልሳንም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤” ተብሎ ተጽፎአልና። እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
Nyochaa ወደ ሮሜ ሰዎች 14:11-12
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1
በእምነት የደከመውንም አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሳትፈርዱበት ተቀበሉት።
Nyochaa ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:4
አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።
Nyochaa ወደ ሮሜ ሰዎች 14:4
Ebe Mmepe Nke Mbụ Nke Ngwá
Akwụkwọ Nsọ
Atụmatụ Ihe Ogụgụ Gasị
Vidiyo Gasị