1
የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ከሕገ ወጥነት ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
Lee anya n'etiti ihe abụọ
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
2
የማቴዎስ ወንጌል 24:14
ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥቱ ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 24:6
ጦርነትንና የጦርነትን ወሬ ትሰማላችሁ፤ አስተውሉ፥ አትደንግጡ፥ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:6
4
የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ ራብና የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ መጀመሪያ ናቸው።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
5
የማቴዎስ ወንጌል 24:35
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:35
6
የማቴዎስ ወንጌል 24:5
ብዙዎች ‘መሢሑ እኔ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:5
7
የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም፤ ስለ ስሜም በሕዝቦች ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጠላላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
8
የማቴዎስ ወንጌል 24:4
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 24:44
ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:44
10
የማቴዎስ ወንጌል 24:42
እንግዲህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ነቅታችሁ ጠብቁ።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:42
11
የማቴዎስ ወንጌል 24:36
“ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአብ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፥ ወልድም ቢሆን፥ ማንም የሚያውቅ የለም።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:36
12
የማቴዎስ ወንጌል 24:24
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳት ታላላቅ ምልክትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
በኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናልና። ከጥፋት ውሃ በፊት በነበሩት ከእነዚያ ቀናት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡ እንደ ነበሩና፥ የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉን እስኪወስድ ድረስ እንዳላወቁት፥ የሰው ልጅ መምጣትም ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
Nyochaa የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
Ebe Mmepe Nke Mbụ Nke Ngwá
Akwụkwọ Nsọ
Atụmatụ Ihe Ogụgụ Gasị
Vidiyo Gasị