1
ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አንድ ሌሊት ዮሴፍ ሕልም አየ፤ ሕልሙን ለወንድሞቹ በነገራቸውም ጊዜ ከቀድሞው ይበልጥ ጠሉት።
Bandingkan
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
2
ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
በስተርጅና የወለደው ስለ ሆነ ያዕቆብ ዮሴፍን ከሌሎች ልጆች ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፤ ስለዚህም ጌጠኛ የሆነ እጀ ጠባብ ሰፋለት።
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
3
ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
ወንድሞቹም አባታቸው ከእነርሱ ይልቅ ዮሴፍን እንደሚወድ ባዩ ጊዜ በመቅናት ጠሉት፤ መልካም ቃልም ሊናገሩት አልወደዱም።
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
4
ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ሌላ ሕልም አይቶ ወንድሞቹን “እነሆ፥ ሌላ ሕልም አየሁ፤ በሕልሜም ፀሐይ፥ ጨረቃና ዐሥራ አንድ ከዋክብት ሰገዱልኝ” አላቸው።
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
5
ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
የዮሴፍ ወንድሞች እጅግ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ እያሰላሰለ ይጠብቀው ነበር።
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
6
ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ፤ እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ የስንዴ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት።”
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
7
ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
ኑ እንግደለውና ከእነዚህ ጒድጓዶች በአንደኛው ውስጥ እንጣለው፤ ከዚህ በኋላ ‘ክፉ አውሬ በላው’ ብለን ማመኻኘት እንችላለን፤ በዚህ ዐይነት የሕልሙን መጨረሻ እናያለን” አሉ።
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
8
ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
9
ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
እርስ በርሳቸውም “እነሆ፥ ያ ሕልም አላሚ መጣ፤
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
10
ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
እነርሱም በሩቅ አዩት፤ ወደ እነርሱም ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ።
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
11
ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
ከምትገድሉት ይልቅ በዚህ በበረሓ ባለው ጒድጓድ ውስጥ ጣሉት” አላቸው። ሮቤል ይህን ያለው ከእጃቸው አድኖ ወደ አባቱ ሊመልሰው ፈልጎ ነው።
Telusuri ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
Beranda
Alkitab
Rencana
Video