1
የማቴዎስ ወንጌል 14:30-31
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ነገር ግን የነፋሱን ብርታት አይቶ ፈራ፤ መስጠም በጀመረም ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ” ብሎ ጮኸ። ኢየሱስም ወዲያው እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ፥ ለምን ተጠራጠርህ?” አለው።
Համեմատել
Ուսումնասիրեք የማቴዎስ ወንጌል 14:30-31
2
የማቴዎስ ወንጌል 14:30
ነገር ግን የነፋሱን ብርታት አይቶ ፈራ፤ መስጠም በጀመረም ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ” ብሎ ጮኸ።
Ուսումնասիրեք የማቴዎስ ወንጌል 14:30
3
የማቴዎስ ወንጌል 14:27
ወዲያው ኢየሱስ ተናገራቸው፥ “አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።
Ուսումնասիրեք የማቴዎስ ወንጌል 14:27
4
የማቴዎስ ወንጌል 14:28-29
ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንህ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” ሲል መለሰለት። እርሱም “ና” አለው። ጴጥሮስም ከጀልባዋ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ በውሃው ላይ ተራመደ።
Ուսումնասիրեք የማቴዎስ ወንጌል 14:28-29
5
የማቴዎስ ወንጌል 14:33
በጀልባዋ የነበሩትም “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።
Ուսումնասիրեք የማቴዎስ ወንጌል 14:33
6
የማቴዎስ ወንጌል 14:16-17
ኢየሱስም “መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው” አላቸው። እነርሱም “ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ ምንም የለንም” አሉት።
Ուսումնասիրեք የማቴዎስ ወንጌል 14:16-17
7
የማቴዎስ ወንጌል 14:18-19
እርሱም “እነዚያን ወደዚህ ወደ እኔ አምጡልኝ” አላቸው። ሕዝቡን በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ።
Ուսումնասիրեք የማቴዎስ ወንጌል 14:18-19
8
የማቴዎስ ወንጌል 14:20
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።
Ուսումնասիրեք የማቴዎስ ወንጌል 14:20
Գլխավոր
Աստվածաշունչ
Ծրագրեր
Տեսանյութեր