1
የዮሐንስ ወንጌል 14:27
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም፤ ልባችሁ አይደንግጥ፤ አትፍሩም።
Compare
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:27
2
የዮሐንስ ወንጌል 14:6
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:6
3
የዮሐንስ ወንጌል 14:1
“ልባችሁ አይደንግጥ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:1
4
የዮሐንስ ወንጌል 14:26
ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:26
5
የዮሐንስ ወንጌል 14:21
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለ የሚጠብቀውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:21
6
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
እኔም አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽናኝ ይልክላችኋል። እርሱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ እናንተ ግን ታውቁታላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ ይኖራልና፤ ያድርባችሁማልና።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
7
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
አብ በወልድ ይከብር ዘንድ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርግላችኋለሁ። በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ያን አደርግላችኋለሁ።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
8
የዮሐንስ ወንጌል 14:15
“ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:15
9
የዮሐንስ ወንጌል 14:2
በአባቴ ቤት ብዙ ማደሪያና ማረፊያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ ቦታ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ እላችሁ ነበር።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:2
10
የዮሐንስ ወንጌል 14:3
ከሄድሁና ቦታ ካዘጋጀሁላችሁም ዳግመኛ እመጣለሁ፤ እናንተም እኔ በአለሁበት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:3
11
የዮሐንስ ወንጌል 14:5
ቶማስም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ የምትሄድበትን የማናውቅ እንግዲህ መንገዱን እንዴት እናውቃለን?” አለው።
Avasta የዮሐንስ ወንጌል 14:5
Home
Bible
Plans
Videod