1
ኦሪት ዘፍጥረት 26:3
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
በዚህች ምድር ተቀመጥ፤ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህችን ምድር ሁሉ ለአንተም፥ ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህም ለአብርሃም የማልሁለትን መሐላ ከአንተ ጋር አጸናለሁ።
Compare
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 26:3
2
ኦሪት ዘፍጥረት 26:4-5
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ይህችንም ምድር ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤ አባትህ አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፤ ትእዛዜንና ፍርዴን፥ ሥርዐቴንና ሕጌንም ጠብቆአልና።”
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 26:4-5
3
ኦሪት ዘፍጥረት 26:22
ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ስለ እርስዋም አልተጣሉትም፤ ስምዋንም “መርኅብ” ብሎ ጠራት፤ እንዲህ ሲል፥ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፤ በምድርም አበዛን።”
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 26:22
4
ኦሪት ዘፍጥረት 26:2
እግዚአብሔርም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው፥ “ወደ ግብፅ አትውረድ፤ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 26:2
5
ኦሪት ዘፍጥረት 26:25
በዚያም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፤ በዚያም ድንኳን ተከለ፤ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 26:25
Home
Bible
Plans
Videod