1
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፥ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፥ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
Compare
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
2
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፥ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
3
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
4
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
ምድርም ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
5
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
6
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
እግዚእብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
7
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
8
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
እግዚአብሔርም አለ፦ “እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፥
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
9
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንደኛ ቀን።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
10
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
እግዚአብሔርም፦ “በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል” አለ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
11
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፥” እንዲሁም ሆነ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
12
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
እግዚአብሔርም አለ፦ “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፥ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፥
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
13
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
14
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ፥ እንዲሁም ሆነ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
15
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
16
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
17
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
እግዚአብሔርም፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
18
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
እግዚእብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፥ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።”
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
19
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
እግዚአብሔርም አለ፦ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
20
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ፦ “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።”
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
21
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
Avasta ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
Home
Bible
Plans
Videod