መጽሐፈ መዝሙር 122
122
ስለ ኢየሩሳሌም የቀረበ ውዳሴ
1“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ!” ባሉኝ ጊዜ
ደስ አለኝ።
2ኢየሩሳሌም ሆይ!
በበሮችሽ ገብተን በውስጥ ቆመናል።
3ኢየሩሳሌም እርስ በርስዋ
ተጠጋግታና ተጠናክራ የተሠራች ከተማ ናት።
4በትእዛዙ መሠረት ለእግዚአብሔር ምስጋና
ለማቅረብ
የእስራኤል ነገዶች ሁሉ የሚሰበሰቡት
ወደዚህች ከተማ ነው።
5ከዳዊት ዘር የነገሡ ሁሉ ሕዝባቸውን ለመዳኘት
በዚህች ከተማ ይቀመጡ ነበር።
6በኢየሩሳሌም ከተማ ሰላም እንዲሆን
እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤
“የሚወዱሽ ሁሉ ይበልጽጉ፤
7በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤
በቤተ መንግሥትሽም ውስጥ ጸጥታ ይኑር።”
8በዘመዶቼና በወዳጆቼ ምክንያት
ኢየሩሳሌምን “ሰላም ከአንቺ ጋር ይሁን!” እላታለሁ።
9ኢየሩሳሌም ሆይ! በአምላካችን በእግዚአብሔር ቤት ምክንያት
ለአንቺ መልካም ነገር እንዲሆንልሽ እመኛለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 122: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 122
122
ስለ ኢየሩሳሌም የቀረበ ውዳሴ
1“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ!” ባሉኝ ጊዜ
ደስ አለኝ።
2ኢየሩሳሌም ሆይ!
በበሮችሽ ገብተን በውስጥ ቆመናል።
3ኢየሩሳሌም እርስ በርስዋ
ተጠጋግታና ተጠናክራ የተሠራች ከተማ ናት።
4በትእዛዙ መሠረት ለእግዚአብሔር ምስጋና
ለማቅረብ
የእስራኤል ነገዶች ሁሉ የሚሰበሰቡት
ወደዚህች ከተማ ነው።
5ከዳዊት ዘር የነገሡ ሁሉ ሕዝባቸውን ለመዳኘት
በዚህች ከተማ ይቀመጡ ነበር።
6በኢየሩሳሌም ከተማ ሰላም እንዲሆን
እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤
“የሚወዱሽ ሁሉ ይበልጽጉ፤
7በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤
በቤተ መንግሥትሽም ውስጥ ጸጥታ ይኑር።”
8በዘመዶቼና በወዳጆቼ ምክንያት
ኢየሩሳሌምን “ሰላም ከአንቺ ጋር ይሁን!” እላታለሁ።
9ኢየሩሳሌም ሆይ! በአምላካችን በእግዚአብሔር ቤት ምክንያት
ለአንቺ መልካም ነገር እንዲሆንልሽ እመኛለሁ።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997