1
ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 1:1
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ ተመልታ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፤ አሕዛብን ትገዛ የነበረች፥ አውራጃዎችንም ትገዛ የነበረች ገባር ሆናለች።
Compare
Explore ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 1:1
2
ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 1:2
ቤት። በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፤ ከሚያፈቅሩአት ሁሉ የሚያጽናናት የለም፤ ወዳጆችዋም ሁሉ ወነጀሉአት፤ ጠላቶችም ሆኑአት።
Explore ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 1:2
3
ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 1:20
ሬስ። አቤቱ! ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፤ መራራ ኀዘን አዝኛለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ አመከነችኝ፤ በቤትም ሞት አለ።
Explore ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 1:20
Home
Bible
Plans
Videos