1
ትንቢተ ኤርምያስ 22:3
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሃአደጉን፥ ባልቴቲቱንም አትበድሉ፤ አታምፁባቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
Compare
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 22:3
2
ትንቢተ ኤርምያስ 22:15-16
በአባትህ ዝግባ አዳራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ አይበላና አይጠጣም ነበርን? ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። የድሃውንና የችግረኛውን ፍርድ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖ ነበር። ይህ እኔን ማወቅ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 22:15-16
3
ትንቢተ ኤርምያስ 22:13
ቤቱን በዐመፅ፥ አዳራሹንም ያለ እውነት ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው ወዮለት!
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 22:13
Home
Bible
Plans
Videos