Psalm 27:1-5

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ ማንን እፈራለሁ? ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣ እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ። ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤ ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ። እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤ እርሷንም እሻለሁ፤ ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣ በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው። በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤ በተቀደሰ ድንኳኑም ውስጥ ይሸሽገኛል፤ በዐለቱ ላይ ከፍ ያደርገኛል።
መዝሙር 27:1-5