ምሳሌ 24:8-9 - Compare All Versions

ምሳሌ 24:8-9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ክፋት የሚያውጠነጥን፣ “ተንኰለኛ” ይባላል። የተላላ ዕቅድ ኀጢአት ነው፤ ሰዎችም ቂልነትን ይጸየፋሉ።

ምሳሌ 24:8-9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ዘወትር ክፋትን ለማድረግ የሚያሤር ሁሉ “ተንኰለኛ” የሚል የቅጽል ስም ይወጣለታል፤ ሞኝ ሁልጊዜ የሚያስበው ኃጢአትን ስለ ማድረግ ነው፤ ፌዘኛን ሰዎች ሁሉ ይጠሉታል።

ምሳሌ 24:8-9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ነገር ግን በአንድነት ያስባሉ፥ ሰነፎችንም ድንገት ሞት ያገኛቸዋል። ሰነፍ በኀጢአት ይሞታል፤ ነፍሰ ገዳይ ሰውን ርኵሰቱ፥

ምሳሌ 24:8-9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ክፉ ለማድረግ የሚያውጠነጥን፥ ተንኰለኛ ይባላል። የሞኝ እቅድ ኃጢአት መሥራት ነው። ሰዎች ፌዘኛውን ይጸየፉታል።