ነህምያ 2:6-9 - Compare All Versions

ነህምያ 2:6-9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚያም ንጉሡ አጠገቡ ከተቀመጠችው ንግሥት ጋራ በመሆን፣ “ጕዞህ ምን ያህል ቀን ይፈጃል? መቼስ ትመለሳለህ?” ሲል ጠየቀኝ። ንጉሡም እኔን ለመስደድ ደስ አለው፤ እኔም ጊዜውን ወሰንሁ። ደግሞም እንዲህ አልሁት፤ “ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆን፣ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ በደኅና እንዲያሳልፉኝ ከኤፍራጥስ ማዶ ላሉት አገረ ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ እንዲሁም ለንጉሡ ደን ጠባቂ ለአሳፍ፣ በቤተ መቅደሱ አጠገብ ላለው ግንብ በሮች፣ ለከተማዪቱ ቅጥርና እኔም ለምገባበት ቤት ሠረገላ የሚሆን ዕንጨት እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይጻፍልኝ፤” መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ ነበረችና ንጉሡም ፈቀደልኝ። ስለዚህ በኤፍራጥስ ማዶ ወደሚገኙት አገረ ገዦች ሄጄ የንጉሡን ደብዳቤዎች ሰጠኋቸው፤ ንጉሡም የጦር አለቆችና ፈረሰኞች ዐብረውኝ እንዲሄዱ አድርጎ ነበር።

ነህምያ 2:6-9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚህን ጊዜ ንግሥቲቱ በንጉሠ ነገሥቱ አጠገብ ተቀምጣ ነበር፤ ንጉሠ ነገሥቱም ጥያቄዬን በመቀበል፦ “ጒዞህ ምን ያኽል ጊዜ ይወስድብሃል? እስከ መቼስ ትመለሳለህ?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም የሚወስድብኝን ጊዜና መቼ እንደምመለስ ነገርኩት። ከዚያም በመቀጠል ወደ ይሁዳ ማለፍ እንዲፈቅዱልኝ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ክፍለ ሀገር ላሉት አገረ ገዢዎች የይለፍ ደብዳቤ እንዲሰጠኝ ለንጉሠ ነገሥቱ ልመና አቀረብኩ፤ እንዲሁም አሳፍ የተባለው፥ የመንግሥት ደን ጠባቂ የሆነው፥ ለቤተ መቅደሱ ቅጽር በርና ለከተማይቱ ቅጽር በሮች ሁሉ እኔም ለማርፍበት ቤት ጭምር መጠበቂያዎች ማሠሪያ የሚሆን የጥድና የዝግባ እንጨት ለመቊረጥ እንዲፈቅድልኝ የሚያዝ ደብዳቤ እንዲሰጠኝም ጠየቅሁ፤ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ስለ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱ የጠየቅሁትን ነገር ሁሉ ሰጠኝ። ንጉሠ ነገሥቱም ጥቂት የጦር መኰንኖችና ፈረሰኞች ከእኔ ጋር እንዲሄዱ አደረገ፤ እኔም ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ወደሚገኘው ክፍለ ሀገር ጒዞዬን ቀጠልኩ፤ እዚያ እንደ ደረስኩም ደብዳቤዎቹን ለአገረ ገዢዎቹ አስረከብኩ፤

ነህምያ 2:6-9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ንግ​ሥ​ቲ​ቱም፦ በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጣ ሳለች ንጉሡ፥ “መን​ገ​ድህ እስከ መቼ ድረስ ይሆ​ናል? መቼስ ትመ​ለ​ሳ​ለህ?” አለኝ። ንጉ​ሡም ይሰ​ድ​ደኝ ዘንድ ደስ አለው፤ እኔም ጊዜ​ውን ነገ​ር​ሁት፤ እር​ሱም አሰ​ና​በ​ተኝ። ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሥ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ ሀገር እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ሱኝ በወ​ንዝ ማዶ ላሉት ገዦች ደብ​ዳቤ ይስ​ጠኝ፤ በቤ​ቱም አጠ​ገብ ላለው ለግ​ንብ በሮች፥ ለከ​ተ​ማ​ውም ቅጥር፥ ለም​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እን​ጨት እን​ዲ​ሰ​ጠኝ ለን​ጉሡ ዱር ጠባቂ ለአ​ሳፍ ደብ​ዳቤ ይሰ​ጠኝ” አል​ሁት። ንጉ​ሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከ​በ​ረች የአ​ም​ላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበ​ረ​ችና። በወ​ን​ዙም ማዶ ወዳ​ሉት ሀገረ ገዦች መጥቼ የን​ጉ​ሡን ደብ​ዳ​ቤ​ዎች ሰጠ​ኋ​ቸው። ንጉ​ሡም ከእኔ ጋር የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለ​ቆ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ልኮ ነበር።

ነህምያ 2:6-9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ንግሥቲቱም በአጠገቡ ተቀምጣ ሳለች ንጉሡ፦ “መንገድህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል? መቼስ ትመለሳለህ?” አለኝ። ንጉሡም ይሰድደኝ ዘንድ ደስ አለው፤ እኔም ዘመኑን ቀጠርሁለት። ንጉሡንም፦ “ንጉሡ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ አገር እንዲያደርሱኝ በወንዝ ማዶ ላሉት አገረ-ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ በቤቱም አጠገብ ላለው ለግንብ በሮች፥ ለከተማውም ቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ለንጉሡ ዱር ጠባቂ ለአሳፍ ደብዳቤ ይሰጠኝ” አልሁት። ንጉሡም በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነችው እንደ አምላኬ እጅ ሰጠኝ። በወንዙም ማዶ ወዳሉት አለቆች መጥቼ የንጉሡን ደብዳቤ ሰጠኋቸው። ንጉሡም ከእኔ ጋር የሠራዊቱን አለቆችና ፈረሰኞች ሰደደ።

ነህምያ 2:6-9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ንግሥቲቱ በአጠገቡ ተቀምጣ ሳለች ንጉሡ፦ “መንገድህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል? መቼስ ትመለሳለህ?” አለኝ። ንጉሡም ሊልከኝ ወደደ፤ እኔም ጊዜውን ወሰኜ ነገርኩት። ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡ መልካም ፈቃዱ ቢሆን፥ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ እንዲያሳልፉኝ ከወንዙ ማዶ ላሉት ገዢዎች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ ለንጉሡ ደን ጠባቂ ለአሳፍ በቤቱ አጠገብ ላለው ምሽግ በሮች፥ ለከተማው ቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይሰጠኝ” አልኩት። ንጉሡም በእኔ ላይ እንዳለችው እንደ አምላኬ መልካም እጅ ሰጠኝ። በወንዙ ማዶ ወዳሉት ገዢዎች ሄጄ የንጉሡን ደብዳቤዎች ሰጠኋቸው። ንጉሡ ከእኔ ጋር የጦር አለቆችና ፈረሰኞች ልኮ ነበር።