ሉቃስ 5:1-7

ሉቃስ 5:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ብዙ ሰዎ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ይሰሙ ነበር፤ እርሱ ግን በጌ​ን​ሴ​ሬጥ ባሕር ወደብ ቁሞ ነበር። በባ​ሕ​ሩም ዳር ሁለት ታን​ኳ​ዎች ቁመው አየ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዓሣ አጥ​ማ​ጆች መረ​ባ​ቸ​ውን ሊያ​ጥቡ ወረዱ። ከሁ​ለቱ ታን​ኳ​ዎች ወደ አን​ዲቱ ታንኳ ወጣ፤ ይቺ​ውም ታንኳ የስ​ም​ዖን ነበ​ረች፤ “ከም​ድር ጥቂት እልፍ አድ​ር​ጋት” አለው፤ በታ​ን​ኳ​ዪ​ቱም ውስጥ ተቀ​ምጦ ሕዝ​ቡን አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው። ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ከፈ​ጸመ በኋላ ስም​ዖ​ንን፥ “ወደ ጥልቁ ባሕር ፈቀቅ በል፤ መረ​ቦ​ቻ​ች​ሁ​ንም ለማ​ጥ​መድ ጣሉ” አለው። ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “መም​ህር፥ ሌሊ​ቱን ሁሉ ደክ​መ​ናል፤ የያ​ዝ​ነ​ውም የለም፤ ነገር ግን ስለ አዘ​ዝ​ኸን መረ​ቦ​ቻ​ች​ንን እን​ጥ​ላ​ለን” አለው። እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸ​ውም ባደ​ረጉ ጊዜ፥ መረቡ እስ​ኪ​ቀ​ደድ ድረስ ብዙ ዓሣ ተያዘ። መጥ​ተ​ውም ይረ​ዱ​አ​ቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነ​በ​ሩ​ትን ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም እስ​ኪ​ጠ​ልቁ ድረስ ሁለ​ቱን ታን​ኳ​ዎች ሞሉ።

ሉቃስ 5:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ሳለ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ቀርበው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ይጋፉ ነበር። እርሱ በባሕሩ ዳር ተጠግተው የቆሙትን ሁለት ጀልባዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ወርደው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። ኢየሱስ ከጀልባዎቹ ወደ አንዲቱ፥ የስምዖን ወደሆነችው ገባ። ስምዖንንም “ይህችን ጀልባ ከምድር ወደ ባሕሩ እስቲ ጥቂት ፈቀቅ አድርግልኝ” አለው። ከዚህም በኋላ በጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር። ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ ስምዖንን፦ “ጀልባዋን ወደ ጥልቁ ባሕር ራቅ አድርገህ አንተና ጓደኞችህ ዓሣ ለማጥመድ መረባችሁን ጣሉ፤” አለው። ስምዖንም “መምህር ሆይ! ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም፤ አንተ ካልክ ግን፥ እነሆ! መረቡን እንጥላለን፤” አለው። መረቡን በጣሉ ጊዜ መረቡ እስኪቀደድ ድረስ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ። ስለዚህ በሌላይቱ ጀልባ ላይ የነበሩት ጓደኞቻቸው መጥተው እንዲያግዙአቸው በጥቅሻ ጠሩአቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱ ጀልባዎች ሊሰምጡ ጥቂት እስኪቀራቸው ድረስ በዓሣ ሞሉአቸው።